የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት

Holy Church

ጥንታዊቷ መጀመርያዊቷ

Lyrics

ጥንታዊቷ መጀመሪያዊቷ

የነቢያት የሐዋርያት

የጻድቃን የሰማዕታት

እምነታችን እንከን የሌላት

ተዋሕዶ ነሽ እምነቲቱ እንከን አልባይቱ

የተስፋው ቃል ኪዳን ዘመኑ ሲፈፀም

አምኖ የዳነብሽ ቀዳማዊው አዳም

እምነቲቷ እንከን አልባይቷ

በሊቃውንቶችሽ ችሎታና ሙያ

ድል የተጎናፀፍሽ በቁስጥንጥንያ

እንደ ዲዮስቆሮስ እንደ አትናቴዎስ

ደጋግመሽ ውለጂ እናት ኦርቶዶክስ

ኃይልና ጥበብን አምላክ ያሳየብሽ

የማዳን ሥልጣኑ በዓለም ያወጀብሽ

ጉባዔ ኒቅያ ጉባዔ ኤፌሶን

አወጁ በዓለም ላይ ተዋሕዶ እምነትን

መጽሐፉ እንደሚለው ሃይማኖት እንዲት ናት

ዋጋ የምታሰጥ የቅዱሳን እናት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening