የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት

Holy Church

ሐዋርያት የሰበኩሽ

Lyrics

ሐዋርያት የሰበኩሽ

ሰማዕታት የሞቱልሽ

ጻድቃንም የከበሩብሽ

ተዋሕዶ ርትዕት ነሽ /2/

መንፈስ ቅዱስ ወዶ ፈቅዶ

ፊልጶስን ጋዛ ሰዶ

ለጃንደረባው ያሰበከሽ

ተዋሕዶ ሃይማኖት ነሽ /2/

የቀደመች ጽኑ መንገድ

የሰማዕታት የጽድቅ እምነት

በሰማይና በምድር ያለሽ

የቅዱሳን ሃይማኖት ነሽ /2/

ጠላት ዲያብሎስ ቢቃወምም

ቀስቱን ቢጨርስ ቢፋለምም

የጸናሽውን በጌታ ደም

የሚረታሽ ማንም የለም /2/

የአትናትዮስ ልዩ ግርማ

የቄርሎስ የሰላማ

የአበው ቅርስ የሊቃውንት

ተዋሕዶ ቅድስት እምነት /2/

የቅዱስ ያሬድ ጥዑም ዜማ

የተክለ ሃይማኖት የገሪማ

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

የጽድቅ የሰላም ነሽ እንግጫ /2/

በቅዱስ ጴጥሮስ መሠረት ላይ

መሥርቶሻል አዶናይ

የኑፋቄ ጦር ቢከፈትም

የገሃነም ደጆች አይችሉሽም /2/

አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት

ወልድ ዋሕድ ሁለት ልደት

ቤተ ክርስቲያን ተሕዋዶ

የሠራልን አምላክ ፈቅዶ

የሰው ልጅ ሁሉ በአንቺ አምኖ

ዘለዓለም ኑሪ ግርማሽ ገኖ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening