✦
የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት
•Holy Church
ሰላም ለኪ
Lyrics
ሰላም ለኪ በሰጊድ ቤተክርስቲያን ሰማይ
ተገለጠ ባንቺ ብርሃነ ፀሐይ
ነሽና ዕንቈ ባሕርይ ሰላም ለኪ
በደመ መለኮት ክቡር የተዋጀሽ
የመንግሥተ ሰማይ መዝገብ ተመስጧል በአንቺ የብፁአን ልብ
ቤተክርስቲያን ማኅደረ ጥበብ ሰላም ለኪ
ለቅዱስ ጴጥሮስ በአደራ የተሰጠሸ በበጎች መንጋ ምሳሌ አማኑኤል ያለሽ በቃሉ አካሌ
ቤተክርስቲያን የምዕመናን ሎሌ ሰላም ለኪ
አመሰገኑሽ ተመስጠው በዝማሬ ሐዋርያተ ሕግ በሙሉ
በማዕድሽ ዙርያ ተሰይመው ሳሉ
የሕይወትን በግ አርደው ስለበሉ ሰላም ለኪ
ማህሌታይ ያሬድ ዘመረልሽ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ
በሥጋ በደሙ ዐይነ ልቡ በርቶ
ድንቅ ምሥጢርን ባንቺ አይቶ ሰላም ለኪ
መጥተናል እኛ ወደ አንቺ ሰልችቶን የኀጢአት ዓለም አልጫው ታሳትፊን ዘንድ ከደምና ሥጋው
ቤተክርስቲያን የነፍስ የሥጋ ጨው ሰላም ለኪ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.