የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት

Holy Church

የቅዱሳን በአት

Lyrics

ልቡና የሚመስጥ መዓዛ እጣኗ

ህሊናን ይገዛል ዝማሬ ድጓዋ

የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው

ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያቸው

የመላእክት ዜማ የአእዋፍ ዝማሬ

የማለቀምበት የትሩፋት ፍሬ

ይዘምሩበታል በአንድነት ተባብረው

የሌዋዊው በትር ጸናጽል ከበሮው

ወራዳዋን ዓለም የናቋት በቅድሚያ

የእምነት አርበኞች ያገኝዋት በፍልሚያ

መውደቂያዬ ይሁን ከመቃብራቸው

ይፈውሳልና ተረፈ አጽማቸው

ከኃጢአት ድንኳን መውጣቴ ነው ዛሬ

የቅዱሳን በዓት ልትሆነኝ ሀገሬ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening