✦
የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት
•Holy Church
ተዋህዶ ሰማያዊት
Lyrics
ተዋህዶ /2/ ሰማያዊት
የፀናች እምነት /2/ ሃሌ ሉያ
ተዋህዶ /2/ መንፈሳዊት
የመንፈስ መብራት /2/ ሃሌ ሉያ
ተዋህዶ /2/ መለኮታዊ
ንጽሕት እምነት /2/ ሃሌ ሉያ
በአንቺ ቢያምኑ /2/ ቅዱሳን
ድልነሱ ሰይጣንን /2/ ሀሌ ሉያ
በአንቺ ቢያምኑ /2/ ሰማዕታት
ተፈተኑ በእሳት /2/ / ሃሌ ሉያ
እንደወርቅ /2/ ተፈትነው
አበራ ገድላቸው /2/ ሃሌ ሉያ
እንኑር /2/ በእምነታችን
በተዋሕዶ መክበሪያችን /2/ ሃሌ ሉያ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.