✦
የቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጋና መዝሙራት
•Holy Church
በሃይማኖት
Lyrics
በጭራሽ እንዲደርቅ የኃጢአት ሥሩ
መበርታት አለበት ሁሉም በምግባሩ
በሃይማኖት /2/ አለብን መፅናት /2/
እንፅና በመንፈስ አንሁን ልበ መንታ
እንዲከፈትልን ደጁን ስንመታ
ሕይወትን የሞሰጥ ወደ አብ የሚወስድ
ከኢየሱስ በቀር የለም ሌላ መንገድ
ምግባራችን አምሮ በእምነት ከፀናን
ሲያበራ ይኖራል የሥራችን ብርሃን
ይብዛ ሠላማችን መልካም ሥራ እንስራ
የመንፈስን ፍሬ ሁላችን እናፍራ.
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.