✦
የሀገራችን የኢትዮጵያ የምስጋና መዝሙራት
•Ethiopia Praise
ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ
Lyrics
ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ ክብርንም ልበሽ በአዲስ ምሥጋና ይመላ ልብሽ
የተወደደ ነው በእግዚአብሔር ሕዝብሽ /2/
ንብረቱ ጠፊ ነው ከንቱ የማይረባ በግፍና ቅሚያ በአመፅ ሲገነባ
ሲሳይሽ ብዙ ነው ከአምላክ የተሰጠሸ በረከት ለማግኘት መስራት ነው ጠንክረሽ
የአህዛብ ብልጽግና አያስቀናሽ ፍፁም ኃላፊ ጠፊ ነው ምኞቱም ዓለሙም
ደመና ነውና ይበናል በቅጽበት በግፍ የተገኘ የተከማቸ ሀብት
ይልቅ በቅንነት በሰላም ለሰራ ሲሳዩ ብዙ ነው ክብሩም አያባራ
ጉቦና ፍትህን ማጣመም እንዳንለምድ ከወንጌሉ ጋራ አለብን መዛመድ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.