የሀገራችን የኢትዮጵያ የምስጋና መዝሙራት

Ethiopia Praise

ተነሽ ኢትዮጵያ

Lyrics

ተነሽ ኢትዮጵያ /3/ እንበል ሃሌ ሉያ

በያሬድ ማኅሌት ተነሽ ኢትዮጵያ

በጣም ተደነቂ ተነሽ ኢትዮጵያ

መሠረት አንቺ ነሸ ተነሽ ኢትዮጵያ

ለዜማ ፈለግ ተነሽ ኢትዮጵያ

ሃሌ ሉያ እያለ ዒለምን የቃኘ ያሬድ ታሪክሽ ነው በረከት ያገኘ

ዕዝልና ግእዙን አራራዩን ቃኝቶ ለልጆችሽ ሰጠ በመንፈስ ተመርቶ

ድፋትና ጭረት ምልክት ምሳሌ ጭረትና ድረት ታጀበው በሃሌ

የሚንቆረቆሩት አንብርና ርክርክ ጸናጽል ከበሮው ተውበው በመድረክ

ድምቀትሽ በእሱ ነው ድጓ ሲታወጅ አንዴም አይጠገብ በተዋሕዶ ደጅ

በያሬድ ዝማሬ መቋሚያ ጸናጽል በዜማ ተመስጧል ንጉስ ገብረ መስቀል

ጸዋትወ ዜማ ሀብትሽ ነው ኢትዮጵያ ስበኪ ወንጌሌን እያልሽ ሃሌ ሉያ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening