✦
የሀገራችን የኢትዮጵያ የምስጋና መዝሙራት
•Ethiopia Praise
የክርስቲያን ደሴት
Lyrics
የክርስቲያን ደሴት የአበው ሃይማኖት ሐዋርያዊት ሀገር ጥንታዊት ናት
የቅዱሳን መንደር የጸሎት ቤታችን ኢትዮጵያ አንቺ ነሽ ቅድስት ሀገራችን /2/
ትነሻለሽ ለፍርድ ወንጌሉን ይዘሽ ለሰሎሞን አምላክ ምስክር የሆንሽ
ሠልጥነሻልና በሃይማኖት ምስጢር ኢትዮጵያ መስክሪ የሥላሴን ክብር /2/
ከእስራኤል ቀጥለሽ አምልኮ ያለሽ የሃይማኖት ሀገር ኢትዮጵያ አንቺ ነሽ
በወንጌሉ ብርሃን ዳግም የተወለድሽ በሥጋ በደሙ ሕይወት የገበየሽ /2/
ጥበብን ለማየት እሥራኤል የሄድሽ በወንጌል ተጽፏል ቀናው እምነትሽ
አይዞሽ ኢትዮጵያ ዘርጊ እጆችሽን ጌታ ይቀበለዋል ንጹህ አምልኮሽን /2/
ሳታይ ያመንሽ ቅድስት ኢትዮጵያ መስቀል ተሸክመሽ አብሪ በዓለም ዙርያ
የተዋህዶን ነገር መስክሪ ለዓለም ጉልበትሽ እኮ ነው ቸሩ መድኃኔዓለም /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.