የቅዱስ ቁርባን ምስጋና መዝሙራት

Holy Communion

ኑ እንቅረብ

Lyrics

ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ /2/ ሥጋውን እንብላ /3/ ደሙንም እንጠጣ

የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው ተሰውቶልናል እንመገበው

እድፉን ኃጢያታችን በንስሓ አንፅተን እንቀበል አምነን በልጅነታችን

መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው በስተእርጅና አይደለም በወጣትነት ነው

ጨረቃና ፀሀይ ደም የለበሱለት ከዋክብተ ሰማይ የተነጠፉለት ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት

ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን

የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ

መጠቁ ተደወለ እንቅረብ በእልልታ በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ

ይችን እድል ፈጥነን እንጠቀምባት ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይባት

አሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ

ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening