የቅዱስ ቁርባን ምስጋና መዝሙራት

Holy Communion

ይህ ቁርባን

Lyrics

ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍፁም ሠማያዊ /2/ እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምደራዊ /2/

ዋ ምን አፍ ነው የሚቀበለው

ዋ ምን ጥርስ ነው የሚያላምጠው

ዋ ምን ሆድ ነው የሚሸከመው

ነበልባል ያለበት የሚያቃጥል ነው

በንፅህና ሆኖ ላልተቀበለው የሚያፍገመግም የሚጎዳ ነው

አምላካችን ሆይ አንተ የቅር ባይ እንደቸርነትህ በደልን አትይ /2/

አሜን አሜን ብለን ተቀብለናል በድፍረትም ሳይሆን በፍርሀት ቀርበናል/2/

ማክበር ይገባናል በንፅህና ሆነን ደፍረን አናቅልለው እንዳያቃጥለን/2/

እንደምታዩት ይህ ቁርባን ፈራጅ ነው እንደሌላው ሳይሆን የተቀደሰ ነው/2/

ሱራፌል ኪሩቤል ፀወርተ መንበር ለመያዝ ያልቻሉት ፈርተውት በክብር/2/

እኛ ተመገብነው አገኘን ድኅነት በነፍስ በሥጋችን ሆነልን ሕይወት/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening