የወርኃ ክረምት መዝሙራት

Rainy Season (Kremit)

ሰማያት ዘምሩ

Lyrics

ዝናማትም ዘነሙ ወንዞችም ጎረፉ /2/ የአምላን ጸጋ እያትረፈረፉ /2/

ሰማያትም ዘመሩ በልዑል ቃለ /2/ የፍጥረታት ሁሉ መጋቢ አንተ ነህ እያሉ /2/

ገበሬውም አረሰ ፈጣሪውን አምኖ /2/ ዘርንም በተነ በምድር ላይ ከጎተራውም ዘግኖ/2/

ደመናትም ዓለምን ይዞራሉ /2/ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ዝናምን ሊያድሉ/2/

በልምላሜ ተዋቡ ዕፅዋት አትክልቱ /2/ ፍሬን ይሰጡ ዘንድ አብዝተው በጊዜው በወቅቱ /2/

መሬትም ከእርሻ አድርጋ ውለታ /2/ የላቡን ወንዙን ከፈለች እንዳዘዘ ጌታ/2/

ድካሙን ጥረቱን አምላክ ተመልክቶ /2/ እንኳን ፍሬ ሰጠው አብዝቶ አድርጎ መቶ/2/

ዝናምን ለዘር ለልምላሜ ፍሬ /2/ የሰጠን አምላክ ይመስገን ይክበር በዝማሬ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening