ትውፊታዊ መዝሙራት

Traditional Hymns

አበባየሆሽ

Lyrics

እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ /2/

ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ

ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን ጌቶች አሉ ብለን

አደይ ቅድስት ሀገሬ እልል በይ /2/

ኢትዮጵያ ለዝናሽማ በዓለም ተሰማ /2/

ለፈጣሪዋ ምስጋና አቅርባ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥተ ሳባ

ጥበቡን አይታ ላደነቀችው ወርቅ ሽቶውን ፅንቍን ሰጠቸው

ንግሥት ሆይ ምስክር ሆንሽ ለሀገርሽ/2/

የአምላክን የፈጣሪያችን ስሙን ጠርተሽ/2/

አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ/2/

ኢትዮጵያ በታሪክሽ ጥንታዊት ነሽ /2/

እንቆቅልሽን ንግሥት ልትፈትን ሄዳ ንግሥተ አዜብ እናት ማክዳ

በልቧ ያለውን አጫወተችው አስቀምጣ አበባ እያሳየችው

መዓዛው የሚሸት የቱ ነው? አለችው

ብለህ ጠቢቡ ለተጠየቀው ከንጉሥ ሰሎሞን አልተሰወረም

መለሰ በእውነት መዓዛው በእውነት

ንግሥት ሆይ ለጥያቄሽ ጥበብ አለሽ /2/

ለሀገር አድባር የሚሆነውን ከልብ ሽተሽ/2/

ኢየሩሳሌም ደርሰሽ መጣሽ እንኳን ለክብር ለዚህ አበቃሽ

ከአምላክ በረከት ፍሬ አግኝተሽ ይዘሽ ስጦታን ዕንቍ ለጣጣሽ

ንግሥት ሆይ በታሪክሽ ከብር ያለሽ /2/

ልጆችሽ አበባየሆሽ እያልን እናስታውስሽ /2/

አደይ ቅድስት ኢትዮጵያ እልል በይ/2/

ኢትዮጵያ በልጆችሽ ደስይበልሽ /2/

አበባው ለምለም ቀጤማው ለምለም ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም /2/

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አለ ብዬ

እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰዎት ብዬ /2/

ይሸታል ዶሮ ዶሮ /2/ ከእማምዬ ጓሮ /2/

ይሸታል የወይን ጠጅ /2/ ከጋሽዬ ደጅ /2/

ከብረው ይቆዩን ከብረው ከዓመት ዐውደ ዓመት ደርሰው /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening