ትውፊታዊ መዝሙራት

Traditional Hymns

ቡሄ በሉ

Lyrics

ቡሄ በሉ ቡሄ በሉ

ሆ የኛማ ጌታ የዓለም ፈጣሪ

ሆ የሰላም አምላክ ትሁት መሐሪ

ሆ በደብረ ታቦር የተገለጠው

ሆ ፊቱ እንደ ፀሀይ በርቶ የታየው

ሆ ልብሱ እንደ ብርሃን ያንጸባረቀው

ድምህን ሰማና በብሩኅ ደመና /2/

የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን /2/

ሆ ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ

ሆ አምላክን አዩት ሙሴ ኤልያስ

ሆ አባትም አለ ልጄን ስሙት

ሆ ቃሌ ነውና የወለድኩት

ሆ ታቦር አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል

ሆ ብርሃን ታየባቸው እጅግ ደስ አላቸው

ሆ የታቦር ተራራ ብርሃነ መለኮት

ሆ በአንቺ ላይ አበራ

ድምህን ሰማና በብሩኅ ደመና /2/

የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን /2/

የአዳም ልጆች ብርሃንን ተቀበሉ

አባቴ ቤት አለኝ ለከት

እናቴም ቤት አለኝ ለከት

አጎቴም ቤት አለኝ ለከት

አክስቴም ቤት አለኝ ለከት

በደብረ ታቦር የተገለጠው

ለሐዋርያት የላከ መንፈስ ዛሬም ለኢትዮጵያ ጸጋውን ያፍስስ

የዓመት ልምዳችን ከጥንት የመጣ

ከመሶብ ይውጣ የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ

ዓመት ዐውደ ዓመት ድገምና ዓመት ድገምና

በጋሽዬ ቤት ያውርድ በረከት ወርቅ ይፍሰስበት

ታሪክ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን

ባሕላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ

እንደ አባቶቻችሁ ችቦውን አብሩት

የቅዱሳን መላእክት የጻድቃን ሰማዕታት

ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening