ትውፊታዊ መዝሙራት

Traditional Hymns

ኢዮሃ አበባዬ

Lyrics

ኢዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ

መስከረም ሲጠባ ተተክሎ ደመራ

ቆስጠንጢኖስ ድል መታ /2/ ነገር ግን መስቀል አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

ክርስቲያኖች እልል በሉ /2/ መስቀል መከታ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

ሀገሪቱን ሲዞር ድካምን ሳይፈራ ተቀብሮ አልቀረም መስቀል ተሸክሞ

ተራራ አፍርሶ ብርሃን እያበራ ጠላት አሳፈረ የመስቀሉ ፍቅር በእኛ ላይ ይደር /2/

መስቀል ሲወጣ ከእናቱ ባጣ መናገሻ እንጦጦ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

ድውይ ሲፈወስ የረር አምባ ቆራ አንካሳ መጣ ሲፈልግ ሰንብቶ

ሙታን ተነሱ የመስቀል ተራራ ይመስገን ጌታ ግሸን ላይ አገኘ

ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ ከአምባሰል ተራራ ግማደ መስቀሉ አርፏል ከዚያ ስፍራ

ህዝበ ኢትዮጵያን እዩት ችቦውን ሲያበራ በታላቁ ብርሃን በመስቀል ደመራ

ይሁን ጋሻችን መስቀል መስቀላችን የክርስቲያን ኃይላችን /2/

የመስቀል ለታ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ በኃጢኣት ጨለማ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

ኢትዮጵያ ኑሪ በእምነት ጸንተሽ ኢትዮጵያውያን ተደስተው

የክርስቶስ መስቀል ብርሃን ሆነልን የባረከሽ በሀገር ልብሳቸው አምረው ደምቀው

መስቀሉን አምነን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

በቃሉ ለምንድን ተሳልመነዋል የእግዚአብሔር ኃይል ነው ከክብሩ ዙፋን

መስቀል ባንዲራችን የነጻነት አርማችን /2/ እርሱ ባርኮናል የመስቀሉ ደመራ እንሰግድለታለን

በኢየሩሳሌም አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ የጸጋ ስግደት አይሁድ አብረው

መስቀል የኛ ጋሻ የድሉን መስቀል የዲያብሎስ ድል መንሻ /2/

የኢትዮጵያ መኩሪያ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

የመስቀሉን ብርሃን በቀራንዮ ጎልጎታ ነጸብራቁን ጠላታችን ድል ተመታ /2/

እፀ መስቀሉ ነው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ ለኛ መከታችን የተሰጠን ለኛ

በመስቀል እንመካለን መስቀለ ክርስቶስ እንድንበታለን /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening