ትውፊታዊ መዝሙራት

Traditional Hymns

ገና ደስታችን

Lyrics

ገና ደስታችን ገና ደስታችን / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

በኢየሩሳሌም ትንቢት ተናግረው / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ተስፋ ስለሰጠው ለአዳም በቀጠሮ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

አብም ልጁን ላከ ቃሉን አክብሮ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ጌታ ተወለደ በቤተልሔም / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ቅድመ ዓለም ንጉሥ አምለክ ዘለዓለም / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

የተወለደው ከድንግል ማርያም / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ዓለምን ለማዳን ለመስጠት ሰላም / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ሰብዐ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

የእስራኤል ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ኮከቡ መራቸው ጌታ ወዳለበት / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ሕጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ለዓለም ፈጣሪ ወድቀው ሰገዱለት / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ለክብሩ ያመጡትን ሳጥኑን ከፈቱት / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

እጣኑን ለክኅነት ወርቁን ለመንግሥቱ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ ያደሩ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

በሜዳ ላይ ያሉ እረኞች ነበሩ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ ነገራቸው / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

መድኃኒት ተወልዷል እርሱም ክርስቶስ ነው / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

የገለጠልንን እንይ ተባባሉ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

የመልአኩን ብሥራት ድንቅ ነው እያሉ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

እረኞችም አዩት ቤተልሔም ደርሰው / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ሕጻንና እናቱን ከዚያው አገኟቸው / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ስብሐት ለእግዚአብሔር ሁላችን በአንድነት / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ሰምተናል ምስጋና ከሰማይ መላእክት / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ሰላም ሰፈነልን በጌታ ልደት / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

አስኪ እልል በሉ ለአምላከ ምሕረት / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ባለተስፋይቱ ኢየሩሳሌም / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ሀገሯ ተወልዶ ቤዛ ኵሉ ዓለም / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ሕዝቦቿ ከናቁት ከከብቶች ግርግም / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

አምላከ ሰላምን አለች አላምንም / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ኢትዮጵያ ሀገራችን ተስፋ ስላደረገች / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

እጅ መንሻን ይዛ ስግደት አቀረበች / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

አንዱን ክርስቶስ ጥንትም ታውቀዋለች / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ቃልም ሥጋ ሆነ ተዋህዶ እያለች / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

በገና ጨዋታ አይቆጣም ጌታ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

በሰላም በፍቅር በንኖር በደስታ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ይገኛል መሐላችን የሠራዊት ጌታ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን

ምስጋና እናቅርብ ሁላችን በእልልታ / ገና ደስታችን ገና ገና ደስታችን /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening