✦
ጠቅላላ
•General
የጽድቅ በር ነሽ
Lyrics
የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማዕታት ምዕራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹህ አክሊላችን
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን/2/
እመቤታችን የእኛ ምርኩዝ ነሽ እመቤታችን ከለላም ሆንሽን
እመቤታችን የእሳት ሙዳይ እመቤታችን እሳት ታቀፍሽ
እመቤታችን በብርሃን ተከበሽ እመቤታችን ወርቅ ለብሰሽ
እመቤታችን ከሴቶች ሁሉ እመቤታችን አብ መረጠሽ
እመቤታችን ድንግል ሆይ ልጆችሽ እመቤታችን ዘውትር ይጠሩሻል
እመቤታችን ስምሽን ለልጅ ልጅ እመቤታችን ያሳስቡልሻል
እመቤታችን በተሰጠሽ ጸጋ እመቤታችን ባማላጅነትሽ
እመቤታችን ምህረትን አሰጪን እመቤታችን ከመሃሪው ልጅሽ
እመቤታችን ያልታረሰች እርሻ እመቤታችን ዘር ያልተዘራባት
እመቤታችን የህይወትን ፍሬ እመቤታችን ሰጠችን የእኛ እናት
እመቤታችን የታረደው መሲ እመቤታችን እናቱን ወደዳት
እመቤታችን በቀኙ ቆማለች እመቤታችን ድንግል እመቤት ናት
እመቤታችን የእውነት ደመና እመቤታችን ዝናብ የታየባት
እመቤታችን ወዳናለች ድንግል እመቤታችን የታተመች ገነት
እመቤታችን ክብር ለሆነችው እመቤታችን ኑ እንዘምርላት
እመቤታችን ደስ ይበልሽ እንበል እመቤታችን የብርሃን እናት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.