ጠቅላላ

General

አማኑኤል ተመስገን

Lyrics

አማን በአማን /2/

አማኑኤል ተመስገን /2/

ለዚህ ፍቅርህ ምን ልክፈል /2/

ድብቁን ሃጢያት አንተ ብትገልጠው

ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው

እንደሰው በቀል ቢኖርህ ጌታ

ለእኔ ሃጢያትስ የለውም ቦታ

በየደቂቃው ሃጢያት ስሰራ

ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ

አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም

በቁጣህ በትር አልገረፍከኝም

ምህረትህን ልከህ አድነኝ ዛሬ

ታክቶኛልና በሃጢያት መኖሬ

ዓለም በሃጢያት እየሳበችኝ

በፍቅርህ በደስታ መኖር አቃተኝ

የሃጢያት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም

ውጤቱ መሮ ፍጹም አይጥምም

እንደ በደሌ ስላልከፈልከኝ

ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening