ጠቅላላ

General

ስለማይነገር ስጦታው

Lyrics

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ቸል ያላለን አምላክ ስንጓዝ ማዕበሉን አቋርጠን

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

የሕይወት እስትንፋስ ዘራብን ህያው እንድንሆን

ይህን ያደረገ አምላካችን እግዚአብሔር ይመስገን

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ንፋስን ገልጾ ማዕበል አቁሞ የሚያሻግር

የዓለም ፈተና ቢበዛ እርሱ መጠጊያችን

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ዳግም እንዳንሞት በሞቱ ሞትን የረታልን

የምንመካበት ትንሳኤን ሰላምን የሰጠን

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ከሲኦል እስራት ተፈተን ነፃ የወጣንበት

መስቀሉን ለሰጠን ለአምላካችን እንዘምር በእውነት

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening