ጠቅላላ

General

የአዋጅ ነጋሪት ቃል

Lyrics

የአዋጅ ነጋሪት ቃል በበረሃ እያለ

የእግዚአብሔር መንገድ አስተካክሉ እያለ

ምስክርነቱን ዮሐንስ አስረዳ

ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን

የደናግል መመኪያ የነብያት ገዳም

አውደ ዓመቱን ባርኪልኝ ድንግል ማርያም /2/

ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና

ካልተስተካከለ መንገድ የለምና

የእግዚአብሔርን መንገድ እንመስርት ሁላችን

ማረፊያ እንዲሆነን ለመጪው ሐብታችን

ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ

ጽድቅና ርህራሄ በእኛ ላይ ይስፋፋ

ስጋና ደምህን በክብር አግኝተናል

ሕይወት እንደሆነን አምላክ ተማጽነናል

ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብሱን

ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን

ከበደላችንም አንጻን አደራህን

በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ልጆችህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening