✦
ጠቅላላ
•General
ውዳሴ ማርያም
Lyrics
ውዳሴ ማርያም እጮሃለሁ
ድንግል እናቴን እጣራለሁ
እንደ አባ ኤፍሬም ነይ ባርኪኝ
ወድሰኒ ልጄ በይኝ
ውዳሴ ማርያም በሰርክ ጸሎት ላይ ውዳሴ ማርያም ዜማ ስናደርስ
ውዳሴ ማርያም ድንግል ትመጣለች ውዳሴ ማርያም በቤተ መቅደስ
ውዳሴ ማርያም የብርሃን ምንጣፍ ውዳሴ ማርያም ከፊቷ ተነጥፏል
ውዳሴ ማርያም ቅዱስ ኤፍሬም ታጥቆ ውዳሴ ማርያም ያመሰግናታል
ውዳሴ ማርያም አባ ህርያቆስ ውዳሴ ማርያም ምስጋና ያደርሳል
ውዳሴ ማርያም የቅዳሴው ዜማ ውዳሴ ማርያም ልብን ይመስጣል
ውዳሴ ማርያም በጎ ነገር ልቤ ውዳሴ ማርያም አወጣ አያለ
ውዳሴ ማርያም ዳዊት በገናውን ውዳሴ ማርያም እየደረደረ
ውዳሴ ማርያም የንጽህናችን ውዳሴ ማርያም መሰረት ነሽና
ውዳሴ ማርያም አንቺን ለማመስገን ውዳሴ ማርያም ልቦናዬ ይጽና
ውዳሴ ማርያም ተፈስሒ ድንግል ውዳሴ ማርያም ኦ ቤተልሔም
ውዳሴ ማርያም ካንቺ ተወለደ ውዳሴ ማርያም መድሃኒዓለም
ውዳሴ ማርያም ቅድሳት ሁሉ ውዳሴ ማርያም አባ ጊዮርጊስም
ውዳሴ ማርያም በወርቅ ዙፋን ላይ ልቤ ተሰወረ ውዳሴ ማርያም ንኢ ድንግል ይላል ተቀምጠሽ ሳይሽ ድንግል በግርማሽ
ውዳሴ ማርያም ዙሪያስን ከበዋል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.