✦
ጠቅላላ
•General
እባክህ ወዴት ነህ
Lyrics
ለመዳኑ ህይወት ለጽድቁ ጠርቼህ
ከዓለም ለይቼ በፍቅሬ መርጬህ
በረከትና ፍቅር ሰላሜን ወርውረህ
ልጁ የምወድህ እባክህ ወዴት ነህ
ይልሃል እግዚአብሔር እባክህ ወዴት ነህ
ከዓለም ጉያ ውስጥ ሽብር ከተሞላው
ከስንጥቅ አለቶች ጎድጓዳ ከሆነው
የአራዊቱ ግርማ የአንበሶቹ ግሳት
የጨለማው ክብደት የፍጥረት ማዛጋት
ከእንዲህ ያለ ስፍራ ተወርውረህ ነወይ
ቀናት ተቆጠሩ አይኖችህን ሳላይ /2/
ከቅዳሴ የወጣ ምስጋና ስቀበል
ጎላ ያለው ድምጽህ ተሰውሮብኛል
በቅድስቱ በኩል በምትቆምበት በቅዳሴ ጊዜ
አይኖቼ ስላጡ ፈልገው ፈልገው ይዞኛል ትካዜ /2/
ልጄ ምን በደልኩህ ምን አጎደልኩብህ
ትተኸኝ የሄድከው እንደዛ ስወድህ
ዘወትር ፊትህን ሳየው ደስ እያለኝ
ደስታዬን በሀዘን ምነው ለወጥክብኝ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.