✦
ጠቅላላ
•General
እኔስ በምግባሬ
Lyrics
እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኛለሁ /2/
እዘኝልኝ ድንግል እለምንሻለሁ /2/
ያንን የእሳት ባህር እንዳላይ አደራ
ድረሽልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ /2/
የዳዊት መሰንቆ የእስራኤል መና
የናሆም መድሃኒት ንኢ በደመና /2/
አንቺ ነሽ ጉልበቴ በደከመኝ ጊዜ
የልቤ መጽናኛ እረዳት ምርኩዜ /2/
አፈሳለሁ እንባ በጣም ተጨንቄ
እማጸንሻለሁ በደሌን አውቄ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.