✦
ጠቅላላ
•General
የሐሰት ዳኝነት
Lyrics
እውነት ስለሆን እየሱስ ክርስቶስ
ዋለ በአደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
ሕይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድን ነው
ከቃሉ እብለትን ባያገኙበትም
ዝምታውን አይተው አላዘኑለትም
ባላወቁት መጠን ጠሉት ካለ በደል
ጥፋቱ ምን ይሆን የሚያደርስ ከመስቀል /2/
የልቡን ትህትና ፍቅሩን ሳያስተውሉ
ቸሩ ጌታችንን አቻኩለው ሰቀሉት
እሩህሩሁን ጌታ አቻኩለው ገደሉት
ሞትን አስወጎዶ ቢሰጣቸው ህይወት /2/
ስለቸርለቱ ስድብን ከፈሉት
ስለርህራሄው የእሾህ አክሊል ሰጡት
ሐሞትና ከርቤ ሆምጣጤ ደባልቀው
መራራ አስጎነጩት ጨክኖ ልባቸው /2/
ፈውስን ለሰጣቸው ልባቸውን ሞልተው
አሉት ወንበዴ ነው ስቀለው ስቀለው
ከእጁ በረከትን የተሻሙ ሁሉ
ይጮኹ ነበር ይገደል እያሉ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.