ጠቅላላ

General

ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ

Lyrics

ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ /3/

የፍቅርን ሕይወት እንድትለብሱ /2/

ሁሉን በሚችል በአምላክ ጥላ

በእረፍት ውሃ ስር አርፈናልና

ሰላምና ፍቅር ህይወት በሚሰጥ

ወደ ጌታችን እንሂድ እንሩጥ

ምህረትና ፍርድ በእጁ የያዘው

የሰላም አባት ወድሃኒዓለም ነው

ህይወት የሆነን በመስቀል ውሎ

ብርሃን ሰጠን ጨለማን ሽሮ

የሚያስደነግጥ የሚያስጨንቀን

ይጠፋልና እርሱን ተማጽነን

በቀን ከሚበር ፍላጻ ሁሉ

ይታደገናል በቅዱስ ቃሉ

እግርህ በድንጋይ እንዳይመታ

በፈተና ውስጥ እንድትበረታ

መቅሰፍት ከቤትህ እንዲከለከል

ይጠብቅሃል ሌሊትና ቀን

ስሙን ያወቀ ህይወት መሆኑን

ይመላለሳል ከሃይል ወደ ሃይል

ረጅም እድሜ ይጠግባል እርሱ

ብርሃን ይሆናል የጸጋ ልብሱ

አቤቱ አንተ ተስፋ ነህና

የምትመግብ የፍቅር መና

ማዳንህ እኛን አስደስቶናል

እንዲህ ያለ ክብር ከየት ይገኛል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening