✦
ጠቅላላ
•General
እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ
Lyrics
እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ ቸርነት አድርገህ /2/
እድሜ ለንስሐ እንደ ህዝቅያስ ሰጥተህ
ጠማማውን ልቤን በቃልህ አቃንተህ
አላውቀውም ብሎ ሲጠየቅ ያመጸው
ዶሮ እስኪጮህ ድረስ ሶስት ጊዜ የካደው
የጅረት ወንዝ ነው የሰጠኸው እንባ
ጴጥሮስ ተጸጽቶ ንስሐ እንዲገባ
ጽዋው እንዳይደርሰኝ የይሁዳ እድል
ልጅህ ሆኖ ውሎ ኃላ መኮብለል
ጴጥሮስ እድለኛው አልቅሶ ተማረ
በትዕቢቱ ይሁዳ እንደወጣ ቀረ
ዘመኗን በሙሉ በዝሙት አቃጥላ
በንስሐ ጠራት ጌታ በገሊላ
ታድሳ ተነሳች በእንባዋ ብዛት
እግሩ ስር ተደፍታ ማርያም መግደላዊት
አመጸኛው ልቤ ዛሬስ መቼ ይተኛል
በሃጢያት በዝሙት በስርቆት ይዋኛል
ወደ ቀድሞ ግብሩ እንዳይመለስ
ፍቅርህ በእኔ ሰርጾ ሃጢያቴን ደምስስ
በደላችን ሁሉ ሳታስብ ትተህ
በምጽአትህ ሰዓት ከጻድቃን ቆጥረህ
ነጭ ልብስን ለብሰን ሆነን ካንተ ጋራ
በሩ ሳይዘጋ አስገባን አደራ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.