✦
ጠቅላላ
•General
በሀዘኔ
Lyrics
በሀዘኔ በጭንቀቴ መጽናኛዬ ነሽ ረዳቴ
እመአምላክ አደራ ድንግል እመቤቴ /2/
ለዓለም ተዘርግቶ እጄ ባዶ ሆኗል
የራሴ ላይ አክሊል ተሽቀንጥሮ ወድቋል
ከኤልዛቤል ሸሽቼ መጣሁኝ ወደ አንቺ
የጎሰቆልኩትን እኔን ተመልከቺ
የእግሬ መሰናክል ለዓለም ደስታ ነው
ተስፋ ቢስ መሆኔ ለጠላቴ ድል ነው
የደስታ መመንጫ የኤልሳቤጥ ዘመድ
እንዳልሰናከል ምሪኝ በመንገድ
ምድር ትለኛለች ተስፋ ቢስ ብቸኛ
ሳለቅስ ሳነባ አይታኛለችና
ከቤተመቅደሱ ለእኔስ ዘመድ አለኝ
በሀዘኔ ሰዓት አይዞህ የምትለኝ
ከአመድ የወደቀ ትንሽ ገንዘብ አለሽ
ልብሽ እራርቶልኝ ፈልጊኝ አጥብቀሽ
እምነቴ እንዳይደክም እንዳልጠፋ ልጅሽ
አድጊያለሁና ከደጀ ሰላምሽ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.