✦
ጠቅላላ
•General
እግዚአብሔርን ጠራሁት
Lyrics
እግዚአብሔርን ጠራሁት በሀዘኔ ጊዜ
እግዚአብሔርን ጠራሁት በጭንቀቴ ጊዜ
አወጣኝ ከጭንቀት ከሀዘን ከትካዜ /2/
የልመናዬን ድምጽ እርሱ ሰምቷልና
ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና
በዘመኔ ሁሉ ስጠራው እኖራለሁ /2/
ጎስቋላ ብሆንም ምስጋና አቀርባለሁ /2/
እንደ ቃልህ መጓዝ መራመድ አቅቶኝ
የሃጢያት መንገድ ማዕበሉ ገፍቶኝ
ወደ እርሱ ስማጸን ደግሞ ስጸጸት /2/
አላሳፈረኝም መጣ በምህረት /2/
ኖህን እንዳዳንከው እኛንም አድነን
ከቀስቱ እንድናመልጥ ምልክትን ስጠን
በትርህ ምርኩዝህ እነሱ ያጽናኑኝ /2/
አንተ ከኔ ጋር ነህ አልፈራም ክፉውን /2/
በበዛ ምህረቱ ያለፈውን ትቶ
በፍቅሩ ጎበኘኝ አልተወኝም ከቶ
ሊቀበለኝ ወዶ ፊቱን አበራልኝ /2/
ማን ይቃወመኛል እግዚአብሔር ካለልኝ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.