ጠቅላላ

General

እርዳኝ ዝም አትበል

Lyrics

እርዳኝ ዝም አትበል የሰራዊት ጌታ

ተስፋ እንደሌለው ሰው ልቤ አያመንታ

አንተን ለማመስገን የነበረኝ ብርታት

ዛሬስ ተስኖኛል አቅቶኛል መትጋት

ጨንቆኝ እጣራለሁ ጸጋ አጣ ህይወቴ

እባክህ አርመኝ እርዳኝ መድሃኒቴ

ልቤ ድንጋይ ሆኖ ቃልህ አልሰበረው

የእጅህን ስራ ጌታዬ አስተካክለው

የክርስትና ኑሮ ስርዓቱን አፍርሼ

አለቅሳለሁ ጌታ በሃጢያት ተከስሼ

ሰላምና ፍቅር ነበር ክርስትና

እኔ ግን ተናወጽኩ አልጸናሁም ገና

ስራዬና ቃልህ አልገናኝ አሉኝ

በጠማማው ልቤ አንተን አሳዘንኩኝ

ጽኑ መሰረት ነው የህይወት አለት

እየተናወጽኩኝ አቃተኝ መጽናት

በእረፍት ውሃ ዘንድ በለመለመው ሳር

በጎችህን ሁሉ በፍቅር የምታኖር

በህይወቴ እንዲታይ የቸርነትህ ክብር

ከደጅህ ተጥዬ ለስምህ ልዘምር

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening