✦
ጠቅላላ
•General
ድንግል እመቤቴ
Lyrics
ድንግል እመቤቴ የህይወቴ ረዳት
የኑሮዬ ጣዕም ዋልታ መሰረት
እለምንሻለሁ /2/ ፍጹም በረከት
ትህትናሽ ሲታሰብ ድንግል እመቤቴ
በሰዎች ልቦና ድንግል እመቤቴ
ግርምትን ይፈጥራል /2/ ልብ ይመስጥና
ጽዮን መጠጊያ ነሽ ድንግል እመቤቴ
የአብርሃም ድንኳን ድንግል እመቤቴ
የታጠረች ተክል /2/ እመብዙሃን
ከሚካኤል ጋራ ድንግል እመቤቴ
ፈጥነሽ ድረሽልኝ ድንግል እመቤቴ
ቅዱስ ገብርኤል ይምጣ /2/ ክብርሽን ያብስረን
ከድንግል ጋር ሆነህ ድንግል እመቤቴ
ኡራኤል ፈጥነህ ና ድንግል እመቤቴ
ሩፋኤል ራጉኤል /2/ ንኡ በደመና
በደማችን ሰርጿል ድንግል እመቤቴ
ፍቅርዋ የማርያም ድንግል እመቤቴ
ምስክር ነን እኛ /2/ እስከ ዘለዓለም
በአባቶች ፋንታ ድንግል እመቤቴ
ልጆችሽ ስላለን ድንግል እመቤቴ
ስምሽን ለልጅ ልጅ /2/ እንዘክራለን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.