✦
ጠቅላላ
•General
ጽረ አርያም
Lyrics
ጽረ አርያም ጽረ አርያም /2/
ክብርሽ ገናና ነው ለዘላለም
በመላዕክት ዓለም በሶስቱ ከተማ
በኤረር በኢዮር እንዲሁም በራማ
ውዳሴ ቀረበ ለሰማይ ንግስት
የአምላክን እናት በክብር አየናት
በበረሃ ያሉ ዓለምን የናቁ
ውዳሴሽን ደግመው ስምሽን የሰነቁ
አንቺን ስንጠራ ተላት ገለል ይላል
ማርያም በግርማሽ ከሳሻችን ያፍራል
ከእግሮቿ በታች ጨረቃን ተጫምታ
የክብርን አክሊል በራሶቿ ላይ ደፍታ
በቅዱሳን ሁሉ ትመሰገናለች
ዓለም የዳነባት ድንግል ማርያም ነች
ብርሃንን ለብሳ በንጽህና አጊጣ
ፍጥረትን ስትባርክ በክብር ተገልጣ
ነፍሳት ተቀደሱ በእምነት ከበዋት
ከበሮን አንስተን እንዘምርላት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.