✦
ጠቅላላ
•General
የጥበብ ሰዎች መጡ
Lyrics
ሰማይና መሬት የማይወስኑት
ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት
ዘጠና ዘጠኙን መላዕክትን ትቶ
አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ
የጥበብ ሰዎች መጡ /2/ ሰምተውት በዜና
እያበራላቸው ኮከብ እንደፋና /2/
ድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ
ለአምላክ ወገኖች መመኪያ የሆንሽ
ካንቺ ተወሰደ የዓለም መድህን
ኩነኔን አጥፍቶ ጽድቅን ሊያወርሰን
ጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም
ሀዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም
እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት
ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት
ሰብአሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ
የእስራኤል ንጉስ ወዴት ነው እያሉ
እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየስርዓቱ
እጣኑን ለክህነት ወርቁን ለመንግስቱ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.