ጠቅላላ

General

ሳር ቅጠሉ ሰርዶ

Lyrics

ሳር ቅጠሉ ሰርዶ ሰንበሌጥ ቄጤማው

በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምለም የነበረው

በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተሞልተው

ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው

እልል በዬ ቤቴልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ /2/

የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ /2/

ያ ትሁት እረኛ የትህትና አባት

ብርሃን ለበሰ በእኩለ ሌሊት

ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ መላዕክት

ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት

እረኝነት ትንሽ የወረደ ግብር

ብሎ ሰው በግምት ደንግጎ ነበር

የብዙ ስው ራስ መሆኑን እረኛ

ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ

የተነበዩለት ነብያት በሙሉ

ጌታ ተወለደ የምስራች በሉ

ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉስ

ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening