✦
ጠቅላላ
•General
ተወለደ
Lyrics
ተወለደ ጌታ ተወለደ /2/
ተወለደ አምላክ ተወለደ /2/
አንዲት ብላቴና የ15 ዓመት ልጅ
ጌታን ወለደችው በመላዕክት አዋጅ
ፍጹም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋህዶ
አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ
ፍጹም ድንግልና ክብር የተሞላች
እንደምን አምላክን በማህፀን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ
አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
በምድር ተፈልጎ እንዳንቺ አልተገኘም
በሀሳብ በግብር ንጹህ ስለሆነች
የአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.