✦
ጠቅላላ
•General
ግነዩ ለእግዚአብሔር
Lyrics
ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር
እስመ ለዓለም ምህረቱ እስመ ለዓለም /2/
እናመስግንሽ የአምላክ እናት በዝማሬ
የዓለም ቤዛ ነውና የማህፀንሽ ፍሬ /2/
በድንግልና የወለድሽው የአንቺ ጽንስ
ለድኩማኖች ብርታት ነው ለህሙማን ፈውስ /2/
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከአንቺ ተወልዶ
መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ /2/
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ
በቸርነቱ አወቀን ከበደል አራቀን /2/
ብርሃነ መለኮት ያደረብሽ አዳራሽ
ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ /2/
ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም ያዘከረ
በመንግስተ ሰማይ ይኖራል እንደተከበረ /2/
እመቤታችን እናታችን ማርያም
የተማጸነሽ ይኖራል ለዘለዓለም /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.