ጠቅላላ

General

ሐይልን በሚሰጠኝ

Lyrics

ሐይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ /2/

መከራም ቢገጥመኝ ለበጎ ነው ብዬ አልፋለሁ /2/

በሰንሰለት አስረው በወህኒ ቢጥሉኝ

መከራን አብዝተው እጅግ ቢያስጨንቁኝ

ለበጎ ነው ብዬ ተስፋ አድርጌሃለሁ

ይሁን አንተ ያልከው እገዛልሃለሁ

ትናንትናም ዛሬም አንተ ያው አንተ ነህ

ፍቅርህ እይቀየር ወረትም የለብህ

ስምህን መጥራቴ ሞገስ ሆኖልኛል

ጠላቴ ቢፎክር መቼ ያሸንፈኛል

በመከራው ጽናት ጉልበቴ ደከመ

ትካዜ ከቦኛል ተስፋዬም ጨለመ

ነገር ቢሆን ባይሆን አንተን እንዳከብር

አደለኝ በጸጋህ ጌታ ያንተን ፍቅር

ከሀገር ወጥቼ በዱር መሰደዴ

ከባዕዳን ሀገር እርቄ መሄዴ

ለበጎ ነውና መቼ ይከፋኛል

ፈጽሞ እንዳልጠፋም ክንድህ ይይዘኛል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening