ጠቅላላ

General

እናመስግነው

Lyrics

እናመስግነው እናመስግነው /2/

አምላካችን ውለታው ብዙ ነው /2/

ከሃጢያት ገደል ከሞት ቤት ጎትቶ

መንግስቱን የሰጠን ከሲኦል አውጥቶ

ዘላለማዊ ቤት ታላቅ ሀብት ያደለን

መቼም የማይተወን ታላቅ አባት አለን

ፍጡራን ቢንቁኝ መጎስቆሌን አይተው

ወዳጆች ቢሸሹኝ ተስፋ ቢስ ነው ብለው

እውነተኛ ረዳት አምላኬ መች ተወኝ

ሁለት እጄን ይዞ ልጄ ተነስ አለኝ

ሞታችንን ሞቶ ህይወቱን ላደለን

ለቸሩ ክርስቶስ ምን እንከፍለዋለን

ለታላቅ ውለታ ጌታ ለዋለልን

በእልልታ እንቀኝ በአንድነት ሆነን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening