ጠቅላላ

General

በሀዘኔ ደራሽ ነሽ

Lyrics

በሀዘኔ ደራሽ ነሽ በጭንቀቴ

በችግሬም ደራሽ ነሽ

የአምላኬ እናት የጌታዬ እናት

ድንግል እመቤቴ ወላዲተ ቃል /2/

መልካሚቱ ርግብ ድንግል እመቤቴ

ማርያም እናቴ ነሽ ድንግል እመቤቴ

ከፍጥረታት ሁሉ ድንግል እመቤቴ

ገናና ነው ክብርሽ ድንግል እመቤቴ

የሀዘኔ መጽናኛ ድንግል እመቤቴ

እንባዬን አባሽ ነሽ ድንግል እመቤቴ

ዋሻ መጠለያ ድንግል እመቤቴ

የዘላለም ቤቴ ድንግል እመቤቴ

መንገድ ስሄድ ስንቄ ድንግል እመቤቴ

መጠጤ ነሽ ምግቤ ድንግል እመቤቴ

እመ አምላክ ስጠራሽ ድንግል እመቤቴ

ይጠፋል እርሃቤ ድንግል እመቤቴ

የእናትነትሽን ድንግል እመቤቴ

ፍቅርሽን አየሁት ድንግል እመቤቴ

ጎጆዬን ስትሞይው ድንግል እመቤቴ

ባዶ የሆነውን ድንግል እመቤቴ

አንቺ እያለሽልኝ ድንግል እመቤቴ

ምን እሆናለሁኝ ድንግል እመቤቴ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening