ጠቅላላ

General

በበጎ ፍቃዱ

Lyrics

በበጎ ፍቃዱ ሁሉ በእርሱ ሆነ /2/

ነገር ሁሉ በእርሱ ተከናወነ /2/

ሰማይና ምድር ግብሩን ተናገሩ

ፈጥሮአቸዋልና እንዲገለጥ ክብሩ

በፈጠረው ፍጥረት የሚታወቅ እርሱ

እግዚአብሔር ይመስገን ስሙን አወድሱ

አልሆነም ያለ እርሱ ፍጹም አንዳች ነገር

ብንመረምረው በሰማይ በምድር

ፈቃዱ ነውና መልካምና በጎ

ፈጥሮ አሳይቶናል ሁሉን ውብ አድርጎ

ክረምትና በጋ ሌሊትና ቀን

ሁሉን አሳይቶ ጌታ አስተማረን

ያደደረገው ሁሉ እንከን የሌለው

ለዚህ ቅዱስ አምላክ ምሳሌም የለው

ያዘነውን ያውቃል ደስም ያለውን

ሁሉ በእርሱ ፈቃድ ስለሚከወን

ችግርና ደስታ ለበጎ ነውና

ይህን ያስተማረን ይድረሰው ምስጋና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening