✦
ጠቅላላ
•General
አንደበቴም ያውጣ
Lyrics
አንደበቴም ያውጣ የምስጋናን ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዓይኔ
በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከሃጢያት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በሐይሉ የዘጋ
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኔ ጋር
በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ
ከቅዱሳኑ ጋር ልዘምር አብሬ
እርሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ
ለጌታዬ ክብር እዘምራለሁኝ
አስፈሪው ነበልባል እሳቱ ቢነድም
ለጣኦት እንድንሰግድ ነገስታት ቢያውጁም
ሁሉ ቢተወኝም ቢጠላኝም ዓለም
ጽናት ይሆነኛል ጌታ መድሃኒዓለም
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.