✦
ጠቅላላ
•General
እልል በሉ
Lyrics
እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
አመስግኑ ለክብሩም ዘምሩለት
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ
በሃጢአት ባርነት ስንኖር ተገዝተን
ከቤቱ ስንርቅ ትዕዛዙን አፍርሰን
አይቶ ዝም ላለን ጠላቶቹ ሳለን
ውለታው ግሩም ነው ክብር ለእርሱ ይሁን /2/
ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን
ስጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም
ምስጋና ይድረሰው ለመድሃኒዓለም /2/
ሕይወቱን የሰዋ እንደ አምላክ ማን አለ
ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ
ፍቅሩ የማይለካ አያልቅም ቢወራ
ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከእኛ ጋራ /2/
ስራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን
ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን
ለማይነገረው ለአምላክ ስጦታ
ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.