ጠቅላላ

General

እግዚአብሔር መልካም ነው

Lyrics

እግዚአብሔር መልካም ነው /2/

በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው /2/

ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን

ሞት ነግሶብን ሳለ በእኛ በሁላችን

ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነው

በመከራው ጊዜ ወሸሸጊያ ሆነው /2/

አብርሃም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት

ከነዓን ሲገባ ሲሰደድ በእምነት

ከተሰጠው ተስፋ አንዳች ሳይጎድልበት

እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት /2/

በሀዘን በችግር በመከራ ጊዜ

ጭንቄን የሚያርቅ ነው የነፍሴን ትካዜ

የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ

እግዚአብሔር መልካም ነው ሀዘኔን አስረሳኝ

የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ

ክርስቶስ ኢየሱስ ሀዘኔን አስረሳኝ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening