ጠቅላላ

General

የያሬድ ውብ ዜማ

Lyrics

የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ /2/

በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ /2/

ምድርና ሰማይ ታምርሽን ይንገሩ

ፍጥረታት በሙሉ ስላንቺ ይመስክሩ

ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ

ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሽ

ማርያም ድንግል እረዳቴ

የምትደርሽልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ

ተአምርሽን በዓይኔ አይቻለሁ

ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ

የእግዚአብሔር ጥበቡ ባንቺ ተገለጠ

የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ

የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ

ለፍጥረት ሁሉ መሰላል የሆንሽ

ነገ ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኝም

አንቺ ካለሽልኝ በፍፁም አልወድቅም

በፊትሽ እንድቆም ለምስጋና

ማርያም ልበልሽ በትህትና

ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም

ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም

አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር

ማርያም /2/ ይበል ተዓምርሽን ይናገር

ጨለማውም ከፊቴ ተገፈፈ

ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ

ከጎኔ ነይ ስልሽ እጽናናለሁ

እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening