ጠቅላላ

General

የማያልፍ የለም

Lyrics

የማያልፍ የለም ሁሉም ያልፋል

ሀዘን መከራም ይታለፋል

የማጣት ዘመን ሁሉም ያልፋል

ሀዘን መከራም ይታለፋል

አንዱን ስሻገር አንዱ ይተካል

ፈታኜ ቀርቦ ፈተና አብዝቷል

ትዕግስት ጽናቱን አድለኝና

ይህም ቀን አልፎ ልይ እንደገና

የማይቻለው በእርሱ ተችሎ

ስንቱ ታለፈ ሁሉ ተጥሎ

በሚያበረታው ጌታ በርትተን

እዚህ ደርሰናል ሁሉንም አልፈን

የማያልፍ መስሎኝ አየሁ አልፌ

የማልችለውን አየሁት ችዬ

ሁሉ ሲያልፍ አየሁ ሁሉን ስትረታ

ምንድነው ዋጋህ ተመስገን ጌታ

ተስፋ ያረኩት ጠፍቷል ከፊቴ

ያስጨንቀኛል ብቸኝነቴ

እኔ አልቻልኩም ጽናት ጎድሎኛል

አልፌ ልየው ያ ይሻለኛል

አይድንም ብሎ ዓለም ወስኖ

ተስፋዬ ጠፍቶ ሁሉ ተከድኖ

በእመ አምላክ ምልጃ አልፌዋለሁ

አስጨናቂውን ድል አድርጌአለሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening