ጠቅላላ

General

ለውዳሴሽ ልትጋ

Lyrics

ለውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ ያለው /2/

እመቤቴ እኸ እመቤቴ ስልሽ እውላለሁ /2/

ከልቤ አቀርባለሁ ምስጋና ለስምሽ

መለመኛዬ ነው ጽኑ ቃል ኪዳንሽ

በሰላምታ ድምፅሽ ያልጸና ማን አለ

ጽንሱ በማህጸን በደስታ ዘለለ

ማርና ወተት ነው የስምሽ ስያሜ

እመቤቴ ስልሽ ይቀላል ሸክሜ

ቅኔ ማህሌቱ ሰዓታት መዝሙሩ

ያመሰግንሻል ምድርና ጠፈሩ

እናቱ ነሽና አንቺ ለአዶናይ

ማለድኩኝ ከፊትሽ ይቅርታውን እንዳይ

ሰዓሊለነ ብዬ ይኸው ተርፌአለሁ

በአንቺ ተደግፌ ነገም እኖራለሁ

ነይ ነይ እልሻለሁ እንደ ካህናቱ

በሰዓታት ጸሎት ቆሜ በሌሊቱ

ዝም አልልም እኔ አወድስሻለሁ

የዓለም መከራ እረሳብሻለሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening