✦
ጠቅላላ
•General
ለእኔስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ
Lyrics
ለእኔስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል /2/
መታመኛዬ እርሱ ነውና ይገባዋል ክብርና ምስጋና
ፍቅሩን እያሰብን እንቅረብ ወደ እርሱ
ይምረናልና መሃሪ ነው እርሱ
በልባችን ይንገስ ይግባ ከቤታችን
የሕይወታችን ዋልታ እርሱ ነው ተስፋችን /2/
ከቶ አላገኝም እርሱን የሚመስል
ነፍሴን የሚያከብራት የሚሰጠኝ ሐይል
በመከራ ሰዓት ከክፉ የሚያድነኝ
ከየት አገኛለሁ መጠጊያ የሚሆነኝ /2/
የለመለመ መስክ መሸሸጊያ ነው
በሰላም ወጥቼ ሰላም እገባለሁ
ተስፋዬ እርሱ ነው ይጠራኛልና
ዘወትር አቀርባለሁ ክብርና ምስጋና
ዘወትር አቀርባለሁ ለአምላኬ ምስጋና
እኔስ ይሻለኛል መቅረብ ወደ ጌታ
ጋሻዬ ነውና የነፍሴ አለኝታ
ስለዚህ እቀርባለሁ አልቀርም ከደጁ
ጠግቤ እኖራለሁ በበረከት እጁ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.