ጠቅላላ

General

ደጅ ጠናሁ

Lyrics

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነምህረትን

ተጽናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን

የአምላክ እናት እመቤታችን /2/

ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን /2/

የመከራው ዘመን አለፈ እንደ ዋዛ

አንቺን ተጠግቼ የዓለሟን ቤዛ

የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት

ባሪያሽን ሰወረኝ ከአስጨናቂው ሞት

እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያ ሁሉ መከራ

እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ

ሰላም ለኪ

ልቤ ባንቺ ጸና ከፍ ከፍም አለ

በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ

በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል

የሐያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል

እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያ ሁሉ መከራ

እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ

ሰላም ለኪ

እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ

በመርገም ምክራቸው ሊለያዩኝ ሲሹ

እርሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው

እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸው

እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያ ሁሉ መከራ

እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ

ሰላም ለኪ

ከአውደ ምህረቱ ሆኜ ስጠራት

ዘንበል ብላ አየችኝ ኪዳነ ምህረት

ሐሳብሽን ምንም የለም የሚመስለው

እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነው

እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያ ሁሉ መከራ

እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ እምዬ ባንቺ ነው የታበሰ

ሰላም ለኪ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening