✦
ጠቅላላ
•General
በመከራ ጽና
Lyrics
በመከራ ጽና በፈተና ጽና /2/
ለጊዜው ነውና ሁሉም ያልፋልና /2/
እዮብ ተጨነቀ በጣም ተማረረ
በመከራው ብዛት ትዕግስትን ተማረ
ልጅ የሌለው ሆነ አጣ ንብረቱን
በመከራ ጸና አልካደም አምላኩን
መፈተን መልካም ነው ያነጥራል እንደ ወርቅ
በመጨረሻው ቀን በክብር እንድንጸድቅ
አንዱን ሳትሻገር ሌላ ቢተካብህ
በሕይወት ዘመንህ ፈተና ቢያጠቃህ
ከአምላክህ ተስማማ እራስህን አዋርድ
በቃሉም ተመራ እንደ ፈቃዱም ሂድ
ዋጋህ ከአምላክህ ዘንድ በሰማይ አለና
በርታ ክርስትያን ሆይ በመከራ ጽና
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.