ጠቅላላ

General

በደልህን አምነህ

Lyrics

በደልህን አምነህ ንስሀ ግባና

ወደ አምላክህ አልቅስ ተጸጸትና

አመስግነው ጌታን አክብረው ከልብህ

በጉብዝናህ ወራት በእርሱ ደስ ይበልህ

ስትቸገር አይቶ ንቆ የማይተውህ

አምላክህን ውደድ እርሱ ነው አለኝታህ /2/

የሃጢያትን ኑሮ አቁምና ዛሬ

ለማፍራት ተነሳ የንስሃን ፍሬ

የእግዚአብሔርን ድምፅ አትናቅ ጥሪውን

ተመለስ ይልሃል አስተውል መንገዱን

የጉብዝናህ ወራት ያበቃል ያከትማል

ድካም መሸነፍም መውደቅም ይመጣል

ተስፋህ ይጨልማል ንብረትህም ያልቃል

ወጣትነትህም መቼ ሁሌ ይኖራል

የወደቅህ ለታ ማንም አያይህም

ሁሉም ሲኖርህ ነው ካንተ ጋር የሚኖር

እስከ መቼ ድረስ እንዲህ ትኖራለህ

መለከት ሲነፋ ወዴት ትደርሳለህ

ለካህኑ ነግረህ የሰራኸውን ሃጢያት

ንስሀ ተቀበል እንድታገኝ ስርየት

ቤትህን አዘጋጅ ክርስቶስ ይመጣል

ማድጋህን ክፈት እርሱም ይሞላዋል

ተመለስ ወደ እርሱ በደሙ ገዝቶሃል

እርሱም አይቀየም ሊቀበልህ ወጥቷል

አመስግነው ጌታን አክብረው ከልብህ

በጉብዝናህ ወራት በእርሱ ደስ ይበልህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening