✦
ጠቅላላ
•General
ወደ አንተ እሰግዳለሁ
Lyrics
ወደ አንተ እሰግዳለሁ ሳለሁ በሕይወቴ
ለአንተም እገዛለሁ እስከ እለተ ሞቴ
አንተ ነህና መድሃኒቴ የዘለዓለም ቤቴ /2/
የነፍስ የስጋዬ የሕይወቴ ቤዛ
አትበለኝ ችላ በደሌ ቢበዛ
አንተን አምኜ እኖራለሁ ወዴት እደርሳለሁ
አንተን አምኜ እኖራለሁ በአንተም እመካለሁ
ሳይመሽብኝ ቀኑ ሳይጨልም ድንገት
በጽድቅ ጎዳና ልጓዝ ወደ ፊት
ምራኝ መንገዱን አሳየኝ እንዳልሳሳት /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.